1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ቤስት ዌስተርን ፕሪሜየር ዳይናሲቲ ሆቴል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሣዉ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመረቀ።
ቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይነስቲ ሶስተኛውን ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በአዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አካባቢ የተገነባ ዓለም ዓቀፍ ሆቴል አግልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን ይፋ አድርጓል።
የአገራችን ሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በቁጥርም ሆነ በጥራት ዓለም ዓቀፍ የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ ከሚፈልገው አቅርቦት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት አዳዲስ አማራጮችን በማካተት የሆቴል ዘርፉን ተቀላቅለናል ሲሉ ወ/ሮ እሌኒ ቀፀላ ገልፀዋል።
ቤስት ዌስተርን ፕሪሜየር ዳይናሲቲ ሆቴል በ1000ካ.ሜ ላይ ያረፈ G+10 ከ3 ቤዝመንት ጋር ያለው ሲሆን 2 ወለል ለመኪና ማቆሚያ ያለው 89 አይነታቸው የተለያየ የእንግዳ መቀበያ ክፍሎ፣ የተለያዩ የመመገቢያ አዳራሾች እና የስፓና ጂም አገልግሎት፣ሁለት የስብሰባ አዳራሽ ፣የቤት ውስጥ መዋኛ ገንዳ፣ ከደህንነት ጋር በተያያዘ (CCTV) ካሜራ፣የጭስ ተቋሚዎች ፣የውሀ መርጫዎች ፣ የእሳት ማጥፊያዎች የሙቀትእና ቅዝቃዜ መቆጣጠሪያ በያንዳንዱ ወለል ይገኛል።
ይህ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በ ሰባት (7) ኣመታት ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሆነ አና ለ አንድ መቶ ሰባ (170) ዜጎች የሰራ እድል የፈጠረ ነው።
ሆቴሉ ቅዳሜ ሀምሌ 08 እና እሁድ ሀምሌ 09 ቀን 2015 ዓ/ም ከ ጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በልዩ ልዩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በመታጀብ ይመረቃል።







